መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትና ክህሎት ስልጠና
መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትና ክህሎት ስልጠና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሙያተኞች ያለ ምንም ክፍያ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቢሮ ስር የሚገኘው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የዲጅታል ሊትሬሲ (መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትና ክህሎት) ስልጠና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሙያተኞች ለ4ኛ ዙር በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን አቅጣጫ በመቀበል በጎንደርና አካባቢው ለሚገኙ 1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ መምህራን፣ ለኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ከ 9 – 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች፣ ለመንግስትም ይሁን ለግል ተቋማት ለሚሰሩ የተለያዩ ሙያተኞች፣ ዘጠነኛ ክፍልና ከዚያ በላይ ለተማሩ ስራ ፈላጊዎች ስልጠናው ያለምንም ክፍያ እየተሰጣቸው እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ፋንታው ገልጸውልናል፡፡
በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ በሚገኘው ኢንፎርማቲክስ ፋካሊቲ በ 14 የተሟሉና ዘመናዊ በሆኑ የኮምፒዩተር መማርያ ክፍሎችና ዲጅታል ላቦራቶሪዎች በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባለቸው የኮምፒዩተር ሳይንስ መምህራን በመታገዝ ስልጠናው በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ አቶ ሰሎሞን አያይዘው ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙ ከ3200 (ከሦሥት ሺ ሁለት መቶ) በላይ ተሳታፊዎች ከነሀሴ 29/2011 ዓ.ም -ጷቅሜ 1 2011 ዓ.ም በ5 ዙር መሰረታዊ የኮምፒዩተር ዕውቀትና ክህሎት ስልጠናቸውን በሚገባ ሰልጥነው በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያጠናቅቁና መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት