በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኮረና ቫይረስን ለመከላክል ድጋፎች ተጠናክረው ቀጥለዋል
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት የእየሰራ የሚገኘው ›› የNala እና Jdc‹‹ ፋውንዴሽን የኮረና ቫይረስን ለመከላከል እንቅስቃሴ ከጀመረ አንድ ወር ተቆጥሯል፡፡ ፕሮጀክቱ ከንክኪ ነፃ የእጅ መታጠቢያ ታንከሮች ጀምሮ የቫይረሱን አስከፊነት በተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ እስከመፈጠር ድረስ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን በሬዲዮ፣ በዌብሳይትና በፌስቡክ አድራሻዎቻችን ለማበረሰቡ ማሳወቃችን የሚታወስ ነው፡፡
ሚያዝያ 26/2012 ዓ.ም ››የNala እና Jdcy‹‹ ፕሮጀክት በሽተኞችን ለሚንከባከቡ ሃኪሞች አገልግሎት የሚውል የ58 ሺህ ብር 8 መቶ 50 የፊት ማስክ፣ 4፣ መቶ 46 ባለ 20 መቶ ሚሊ ሊትር ሳኒታይዘርና 9 ሺህ 8 መቶ የእጅ ጓንት ለጎንደር ጤና መምሪያ በስጦታ ማስረከቡን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር መኩሪያው ዓለማየሁ ገልጸዋል፡፡
በርክክብ ሥነሥርዓቱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲቫ ኢንጂነር ማስተዋል ስዩም፣ የጎንደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ገቢያው አሻግሬና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያያጅ ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው ተገኝተዋል፡፡
በተመሳሳይ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ በመስራት የሚታወቀው የነገ ተስፋ በጎአድራጎት ብሮጀክት በቀጥታ ንክኪ ላላቸው ሀኪሞች የሚውል የ75 ሺህ ብር 3 መቶ 50 N-95 የፊት ማስክ ለጤና መምሪያው በስጦታ ማበርከቱን የበጎአድራጎት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ወ/ሪት ንግስት ገ/ስላሴ ገልጸዋል፡፡
የሕዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት