የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለመሰናዶ ትምህርት ቤት መምህራን ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጠፈጥሮና ቀመር ሳይንሰ ኮሌጅ የስታቲስቲክስ ትምህርት ክፍል ለ3 ተከታታይ ቀናት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በስታትስቲክስ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አራጋው እሸቴና ጓኞቻቸው ሲሆኑ፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ የመሰናዶ ትምህርት ቤት መምህራንን አቅም በማጎልበት በያዝነው የትምህርት ዓመት በቂ አገልጋሎት እንዲሰጡ ለማድግ መሆኑን ከስልጠናው መረዳት ተችሏል፡፡ ስልጠናው መሰረት ያደረገው የስታትስቲክስ ሶፍትዌርን በአግባቡ የመጠቀም አቀምን ከፍ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳለጥ ሲሆን በጭልጋ፣ ገንዳውሃና ቆላድባ ከተማ ለሚገኙ የመሰናዶ ትም/ቤቶች 30 መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ሀገራችን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!********************************************************
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም
