Book Launch “Culture of Democracy-From Theory to Lived experience” በሚል የፓናል ውይይት ተካሄደ
“Friedrich Ebert” ስፖንሰርነት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ የሲቪክስ ትምህርት ክፍል ባዘጋጀው የውይይት ፕሮግራም Book Launch “Culture of Democracy -From Theory to Lived experience” በሚል የፓናል ውይይት ጥር ነ03/2010ዓ.ም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ህንፃ በማኔጅመንት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡በፓናል ውይይቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ ደሳለኝ መንገሻን ጨምሮ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ መምህራን፣የስነዜጋና ስነምግባር ተማሪዎችና የፍልስፍና ሙሁር የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና ሌሎች በርካታ ሙሁራን ተገኝተዋል፡፡አቶ ቴዎደሮስ አቡሃይ በስነዜጋና ስነምግባር ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰርና በማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ የሬጅስትራር ሃላፊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በኋላ የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ባደረጉት ንግግር በምርምርና በጥናት የተደገፈ መጽሐፍ መዘጋጀቱና ውይይት መደረጉ ለምህራን፣ለተማሪዎች ብሎም ለሀገር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡በቀጣይም በዲሞክራሲ ባህል ታሪክ ላይ የሚዘጋጁ መጽሐፍት በጥናት የተረጋገጡና ሀገራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸው ገለፀው Book Launch “Culture of Democracy-From Theory to Lived experience” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው መጽሓፍ ላይ በማረምና በማስተካከል ለተሳተፉት ሙሁራን መሰጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
[widgetkit id=8086]
የፓናል ውይይቱ የተመራው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ም/ፕሬዚደንት በሆኑት በዶ/ር ሙሉቀን አዳነ፣በዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ በሶሾሎጂ መምህር ዶ/ር ቡሻ ትአና በስነዜጋና ስነምግባር መምህር ዶ/ር ሶንጃ ጆን ሲሆን ለመወያያ በቀረበው የጥናትና ምርምር መጽሀፍ ላይ በማረምና በማስተካከል የተሳተፉ ናቸው፡፡
በመድረክ የቀረበው የውይይት መነሻ ሀሳብ የደሞክራሲ ባህልን መገምባት የህግ የበላይነትን መገመባት እንደሆነ፣ደሞክራሲ ባህልን መከተል አገራዊ አንድነትን ለማምጣት ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑ፣ደሞክራሲ ባህልን ስንጠቀም እንደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ መሆን እንዳለበት፣በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ባህልን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ መምራት አለመቻልና ሌሎች ሃሳቦችም በሰፊው ተነስተው ውይይትና ክርክር ከተካሄደባቸው በኋላ ስምምነት ላይ በመድረስ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
ዘጋቢ፡- በላይ መስፍን
የሕ/ዓ/አ/ገ/ዳይሬክቶሬት