ሀምሌ 22/2011ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ቀን በሚል የችግኝ ተከላ ተካሂዷል
ሀምሌ 22/2011 ዓ.ም አረንጓዴ
አሻራችን እናሳርፍ የሚለውን አገራዊ አጀንዳ ታሳቢ በማድረግ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ምንዝሮ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በፕሮግራሙ የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ የአማራክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት አፀደወይን፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ሌሎቾ የፌደራል፣የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

በ6.3 ሄክታር ቦታ ላይ 16 ሺህ ችግኝ የተተከለ ሲሆን ክብርት ወ/ሮ ሳሀለወርቅ ዘውዴና ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተዟዙረው ጉብኝተዋል፡፡



