ሀገር አቀፍ የካሪክለም ግምገማ ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ሁለት የማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራሞች ማለትም በጥምር ደን ግብርና እና በተቀናጀ የተፋስስ አያያዝ (MSc in Agroforestry and MSc in Integrated Watershed Management) ፣ በ3ኛ ዲግሪ ደግሞ በግብርና ምጣኔ ሀብት (PHD in Agricultural Economy)ፕሮግራሞችን ለመክፈት ታህሳስ 20/2013ዓ/ም ሀገር አቀፍ የካሪክለም ግምገማ በጠዳ ግቢ አልጣሽ አዳራሽ አካሄደ፡፡
በዕለቱ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ከሃሊ ጀምበሬ፣ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ዳረጎት፣ ከአዲስ አበባ ሜትሮፖሊቲያን ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ደግዬ ጎሹ፣ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ዘበነ አስፋው፣ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ጌታ ዘለቀ፣ የኮሌጁ መምህራን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኘንተዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ከሃሊ ጀንበሬ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣በንግግራቸውም ኮሌጁ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት በርካታ ስራዎችን መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡ዶ/ር ከሃሊ አያይዘውም ኮሌጁ ፈጣን እድገት ካስመዘገቡ በሀገሪቱ ካሉ የግብርና ኮሌጆች መካከል የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን በመክፈት አንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የጎንደር ዩኒቨርሲቲን የምርምር ዩኒቨርሲቲ አድርጎ ከመለየቱ ጋር ተያይዞ አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች እንዲከፈቱና ሌሎች የምርምር ስራዎችም እንዲሰሩ ሰፊ እድልን ስለሚሰጥ የዕለቱ መርሃ ግብር ወቅቱን የጠበቀና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኮሌጁ መምህራን ለግምገማው መነሻ የሚሆን ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን፣ በዶ/ር ማረልኝ አዱኛ በግብርና ምጣኔ ሀብት (Agricultural Economy)፣ በመምህር ዳግም ፍቅር በጥምር ደን ግብርና (Agroforestry )እና በመምህር ማስረሻ አሸናፊ በተቀናጀ የተፋስስ አያያዝ (Integrated Watershed Management)በሶስት የተለያዩ አዳራሾች ቀርቧል፡፡ በመቀጠልም በውጭ ገምጋሚዎች ውይይቱ እና ግምገማው ተካሂዷል፡፡
ኮሌጁ አሁን ላይ ስድስት የመጀመሪያ ዲግሪ፣ አስራ አንድ ሁለተኛ ዲግሪና ሶሰት የፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞች ያሉት ሲሆን፣ ወደፊትም ይህንን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ለመክፈት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
*****************************************************************************************
ሀጋራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኑነት ዳይሬክቶሬት
ታህሳስ 20/2013 ዓ.ም







