ለህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ አዲስ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ በአጠቃላይ የሬጅስትራር ህጎችና የተማሪ ዲሲፕሊን በተመለከተ ለአዲስ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ህዳር 25/2013 ዓ.ም ተሰጠ፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ የትም/ ክፍል ኃላፊዎችና በርካታ አዲስ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የምርምር ተቋም መባሉን የጠቀሱት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና አጠ/ስፔ/ሆስፒታሉ አካ/ዳይሬክተር ዶ/ር አስማማው አጥናፉ፣ ምርምር ላይ ትኩረት ለማድረግ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን የማስፋፋት ስራ እንደሚሰራ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው አንስተዋል፡፡
በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን የሚመለከቱ በአጠቃላይ የሬጅስትራር ሀጎች እና የተማሪ ዲሲፕሊንና የኮቪድ- 19 መመሪያ እንዲሁም ተቋሙ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ከመመረጡ አንጻር የመማር ማስተማር ትኩረቱ ምን መምስል እንዳበት የሚገልጹ ማብራሪያዎች በተለያዩ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የቀረቡ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡትም በዩኒቨርሲቲው የድህረ-ምረቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፕ/ር ታደሰ አወቀ፣ በህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ ረ/ሬጅስትራር ኃላፊ አቶ ችሎት ደስታ እና በኮሌጁ የተማሪዎች ዲን አቶ አብርሀም ታረቀኝ ናቸው፡፡ በተለይም ከሬጅስትራር አሰራር ጋር በተያያዘ ከመጀመሪያ ዲግሪ ህጎች በተወሰነ መልኩ የተለዩ የድህረ ምረቃ አሰራሮች ስለሚኖሩ በነዚህ ህጎች ላይ ግንዛቤ መፍጠር ተማሪዎች ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል እንደሚረዳ አቶ ችሎት አብራርተዋል፡፡
የቀረቡትን ገለጻዎች ተከትሎም ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፤ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውም ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
***********************************************************
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ህዳር 25/2013 ዓ.ም







