ለቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት
የዩኒቨርሲቲያችን አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት
ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ለሁሉም ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት አሰጣጥን በተመለከተ ዛሬ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ተማሪና መምህር ፊት ለፊት ተገናኝተው መማር ማስተማሩ ወደ ክፍል እስኪመለስ እና ከኮረና ቫይረስ (COVID-19) ስጋት ነፃ እስክንወጣ ድረስ የተስተጓጎለውን ትምህርት አማራጭ መንገዶችን ተጠቅሞ ማስኬድ እንደሚገባ በአገር ዓቀፍ ደረጃ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ባላችሁበት ሁሉ ሰላምና ጤና አብዝተን የምንመኝላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን የሚከተሉትን ተግባራት እንድታደርጉ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
1ኛ. የቅድመ ምረቃ (የመጀመሪያ ዲግሪ) መደበኛ ተማሪዎች የተጫኑና ወደፊትም የሚጫኑ የትምህርት መርጃዎችን በ ድረ ገፅ https://ndl.ethernet.edu.et የምታገኙ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አብዛኞቹ መማሪያ ቁሳቁሶች (Course materials) ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገፅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ስለተጫኑ ተማሪዎቻችን እየገባችሁ በማውረድ (Download በማድረግ) ማንበብ አለባችሁ፡፡

ሳትዘናጉ የተጫነላችሁን(upload የተደረገላችሁን) የኮርስ መማሪያዎች (materials) በትክክል ካጠናችሁና ካነበባችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲያችሁ በምትመለሱበት ሰዓት የአጭር ጊዜ ማካከሻ ትምህርት ተሰጥቷችሁ ለፈተና የምትቀርቡና ተመራቂዎች ለምረቃ፣ ሌሎቻችሁ ወደ ቀጣዩ ደረጃ (ዓመት) ትሸጋገራላችሁ፡፡
2ኛ. የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በ እና ከአማካሪዎቻችሁ ጋር እየተገናኛችሁ የመመረቂያ ፅሁፎቻችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም እንደ ኢሜይል፣ ቴሌግራም፣ስካይፒ፣ ዋትስ አፕ፣ቫይበርና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎችን ተጠቅማችሁ የምርመር ስራዎቻችሁን መስራት ይኖርባችኀል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ በተገቢው መንገድ ጥናታዊ ፅሁፋችሁን ከአማካሪዎቻችሁ ጋር እየተወያያችሁ ጨርሳችሁ በonline የምታቀርቡ ሲሆን የዚህ ዓመት ምረቃ መርሃ ግብራችን የተጠበቀ መሆኑን ማስታወስ እንወዳለን፡፡
3ኛ. የተከታታይ ኘሮግራም ተማሪዎች ባላችሁበት ሆናችሁ ከአሁን በፊት የወሰዳችሁትን የኮርስ መማሪያ (course material)፣ ያልወሰዳችሁ ደግሞ በክፍል ተወካዮቻችሁ አማካይነት ከመምህራን፣ ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ፣ ኮሌጅ ዲኖች እንዲሁም ከተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክተር ጋር እየተመካከራችሁ ሞጁሎቻችሁን እና መማሪያ ፅሁፎችን በመውሰድ እንድታጠኑ እንዲሁም ከላይ በተራ ቁጥር 1 በተገለጸው መሠረትም ማቴሪያሎችን በማውረድ እንዲትጠቀሙ እያሳሰብን የአጭር ማካካሻ ትምህርት ተሰጥቷችሁ፣ ፈተናዎችንም ወስዳችሁ ወደ ቀጣዩ ሴሚስቴር የምትሸጋገሩ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
✍ማስታወሻ፡
::::::::::::::::::::::
ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጡ አቅጣጫዎችንም ሆነ ዩኒቨርሲቲያችን አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩት ቴሌቪዥን፣ሬዲዮ፣ድረ ገፅ እና ፌስቡክ አድራሻችን የምንገልፅ ይሆናል፡፡
ድረ ገፅ፡ www.uog.edu.et
ፌስቡክ፡@TheUniversityofGondar
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት
ሚያዚያ24/2012 ዓ.ም



