ምሁራንና ማህበረሰቡ በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሀገር እድገት የሚጠቅም ክህሎትና እውቀት ያላቸውን ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ በርካታ ምሁራንን በተለያየ ጊዚያት በመጋበዝ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ተማሪዎችና ሰራተኞች ትምህርታዊ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ከሀገር ውጪ በምህንድስና ዘርፍና ተያያዥ ሙያዎች ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ኢንጅኔር ባንቲሁን ትዛዙን በመጋበዝ፣ “ለፈጣን ለውጥ የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ከህዝብ ጋር ማጣመር /Engaging the University Communities with the People for a Leap Change/” በሚል የውይይት ርዕስ ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎች ትምህርታዊ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ሙሩቃን ለምን ስራ ያጣሉ፣ ስራና ሰራተኛን ለማገናኘት የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ምን መሆን አለበት፣ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን አቅም በተገቢው ሁኔታ በማሳደግና ለገብያ በማቅረብ በኩል ምን ምን ጉድለቶች ይስተዋላሉ? የሚሉና ተያያዥ የሆኑ ነጥቦች በውይይቱ በስፋት ተዳሰዋል፡፡
ስልጠናው የተካሄደው መስከረም 7/2012 ዓ.ም በማራኪ ግቢ አልሙኒየም ህንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት የሆኑትን ፕ/ር መርሻ ጫኔን ጮምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡
ፕ/ር መርሻ የዩኒቨርሲቲው መምህራን በአብዛኛው ወጣት መሆናቸውን አውስተው፣ ወጣት ምሁራን እንደ ኢንጅነር ባንቱሁን ካሉ ከፍተኛ ልምድ ካካበቱ ምሁራን እውቀትና ልምድን በመቅሰም ማህበረሰብን ብሎም ሀገርን ሊለውጡ በሚችሉ ተግባራት በስፋት መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡