ሶስተኛው ዙር የገርልስ ካን ኮድ/girls can code/ ሰልጣኞች የፕሮጀክት ስራቸውን አቀረቡ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመረጃና ግንኙነት ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በገርልስ ካን ኮድ ፕሮግራም ለ ሁለት ወር ስልጠናቸውን ሲከታታሉ የነበሩ በጎንደር ከተማ በተለያዩ ት/ቤቶች የተመለመሉ 35 ሴት የ2ኛ ደረጃና የመሰናዶ ተማሪዎች፣ የፕሮጀክት ስራቸውን መስከረም 9/2012 ዓ.ም በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ ድህረ ምረቃ ፕሮግራም መሰብሰቢያ አዳራሽ አቅርበዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ረዳት አቶ ዳዊት ዳርጌ፣ የዩኒቨርሲቲው የመረጃና ግንኙነት ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኃይለማርያም ቀሬ፣ ስልጠናውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች እንዲሁም አሰልጣኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ገርልስ ካን ኮድ የተሰኘው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በዩኒቨርሲቲው የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ከተጀመረ 3ኛ ዓመቱ መሆኑን የገለጹልን የፕሮግራሙ አስተባባሪና በዩኒቨርሲቲው አይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ኔትወርክ አድሚኒስትሬተር አቶ እሱያውቃል ሲሳይ ናቸው፡፡ የስልጠናው ዓለማ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ሴት ተማሪዎችን በኮምፒዩተር ክህሎት ማለትም በመሰረታዊ ኮምፒዩተር፣ በኔት ወርኪንግ፣ በዌብሳይት ዲዛይንና በኮዲንግ የተሻለ ዕውቀት እንዲኖራቸው ማስቻልና ሴት ተማሪዎች ከቴክኖሎጂ ጋር ይበልጥ እንዲቀራረቡ ለማስቻል እንደሆነ አቶ እሱያውቃል ገልጸዋል፡፡ አቶ አሱያውቃል አያይዘውም ይህ የኮምፒዩተር ስልጠና ሴት የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የበጋ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በክረምት ወቅት በረፍት ጊዚያቸው ያለምንም ክፍያ እንደሚሰጥ አውስተው፣ ተማሪዎች በረፍት ጊዚያቸው ከዘመኑ ጋር ሊያራምድ የሚችል ስልጠና ከማግኘታቸውም በላይ ትርፍ ጊዜአቸውን በአልባሌ ቦታ እንዳያሳልፉ ይራዳልም ብለዋል፡፡

በዕለቱ በሰልጣኞች የተሰሩ የተመረጡ የፕሮጀክት ስራዎች የቀረቡ ሲሆን የፕሮጀክት ስራዎቹም ለሀገር እድገት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውና የተማሪዎቹን አቅም ያሳዩ መሆናቸውን ለማየት ችለናል፡፡ የቀረቡት ፕሮጀክቶችን መሰረት በማድረግ የተማሪ ወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ሁኔታዎችን ላመቻቸው ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የኮምፑዩተር እውቀትንና ክህሎትን በላቀ ሁኔታ ላስተማሯቸው መምህራን ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች በስልጠናው ሂደት መደሰታቸውንና ስለ ኮምፒዩተር ክህሎትና ተያያዥ ስለሆኑ ጉዳዮች በቂ መሰረት እንዳገኙ ገልጸውልናል፡፡
በመጨረሻ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በሚገባ ማጠናቀቃቸውን የሚገልጽ ሰርቲፊኬት በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ረዳት በሆኑት በአቶ ዳዊት ዳርጌ እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡