በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ “Systematic Review and Meta Analysis” ላይ የምርምር ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡

በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አስማማው አጥናፉ እንደገለፁት “ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ቀጣይ ስልጠናዎች ለመምህራን ፣ለጤና ባለሙያዎችና ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ለመስጠት መታቀዱን አስታውሰዋል፡፡

በመክፈቻ ንግግር ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲያችን የምርምርና ህትመት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ዘውዱ ተሾመ ” በተለይ የህክምና ባለሙያዎች በማህረሰብ አገልግሎት እና መማር ማስተማሩ ላይ የሚጫወቱትን ጉልህ ሚና በምርምር ተሳትፎም አጠንክረው እንዲሰሩበት አሳስበዋል ፡፡ ዳይሬክቶሬቱም በዚህ ዓመት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የ”Systematic Review and Meta Analysis” ስልጠና ከ40 በላይ የጤና ባለሙያዎችና መምህራን ይሳተፉበታል፡፡ ለተመራማሪዎች የመረጃ አሰባሰብ፣አተናተንና ግኝት አቀማመር እውቀትን ከማሳደጉ ባሻገር ቀደም ብለው የተሰሩ ምርምር ውጤቶችን በቀላሉ ለማግኘትና ክፍተቶችን ለመለየት ያግዛል ፡፡ እንዲሁም የተመራማሪዎችን አቅምና ተሳትፎ በማሳደግ ጥናታዊ ህትመቶችን ለተጠቃሚ ተደራሽ በማድረግ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት



