በምህንድስና ዘርፎች የስርአተ-ትምህርት ግምገማ ተካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው መካኒካል ኢንጅነሪንግ ት/ክፍል በሶስት የምህንድስና ዘርፎች (3ኛ ዲግሪ በተርማል ኢንጅነሪንግ (PhD in Thermal Engineering)፣ 2ኛ ዲግሪ በአውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ (MSc in Automotive Engineering) እንዲሁም 2ኛ ዲግሪ በማተሪያል ኢንጅነሪንግ (MSc in Material Engineering) የስርአተ-ትምህርት ግምገማ አውደ ጥናት ዛሬ ሰኔ 22/2013 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን መስፍን፣ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች መከታተያ ዳይሬክተር ዶ/ር አስማማው አለሙ፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ገምጋሚዎችና የኢንስቲትዩቱ መምህራን በመርሀ-ግብሩ ተሳትፈዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት 9 የቅድመ-ምረቃና 6 የድሀረ ምረቃ ፕሮግራሞች በኢንስቲትዩቱ ተከፍተው ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተማር ላይ እንደሚገኙ አቶ ሰሎሞን በመክፈቻ ንግግራቸው አውስተዋል፡፡ በተመሳሳይ በተለያዩ የምህንድሰና ድህረ ምረቃ ዘርፎች የስራዓተ ትምህርት ግምገማዎችን በማካሄድ በ3ኛ ድግሪ- ብዛት 3 እንዲሁም በ2ኛ ዲግሪ- ብዛት 8፣ በአጠቃላይ 11 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች በሚቀጥለው የትምርህርት ዘመን እንደሚከፈቱ ዳይሬክተሩ አያይዘው ተናግረዋል፡፡




