በምርምር ስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
በምርምር ስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
* * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * *
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢፒዲሚዮሎጅና ባዮ-ስታትስቲክስ ትም/ክፍል የምርምር ስነምግባርን በተመለከተ ለ”ጆርናል ክለብ” አባላት አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ህዳር 03/2013 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኢፒዲሚዮሎጅና ባዮ-ስታትስቲክስ ትም/ክፍል የተቋቋመው ”ጆርናል ክለብ” በዩኒቨርሲቲው የምርምር አቅምን ለማጎልበት ታስቦ ተቋቋመ ክበብ ነው፡፡
የምርምር ስነ-ምግባርን በተመለከተ በእለቱ ጽሁፍ ያቀረቡት ኢፒዲሚዮሎጅና ባዮ-ስታትስቲክስ ትም/ክፍል መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕ/ር እጅጉ ገበየሁ፣ በተለያዩ አጥኝወች የሚሰሩ የምርምር ስራዎች አልፎ አልፎ ከምርምር ስነ-ምግባር አንጻር ግድፈት አንደሚታይባቸው ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም አንድ ጥናት አድራጊ የምርምር መርህን በመከተል የተሳታፊዎችን መብትና ደህንነት የጠበቀ፣ የተጠቀመባቸውን የጥናት ምንጮች በአግባቡ የገለጸ እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግር መሰረት ያደረገ ጥናት መስራት እንደሚገባው አብራርተዋል ፡፡
እንዲህ አይነት መድረኮች መፈጠራቸው በተለያየ ደረጃ በሚማሩ ተማሪዎች፣ በሲኒየር መምህራንና ሌሎች አባላት መካከል በምርምር ስነ ምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እውቀትና ልምድ ልውውጥ በማድረግ፣ የምርምር መርህን በመከተል ለማህበረሰቡ ጠቃሚ ጥናት ለማድረግ እንደሚያግዝ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኢፒዲሚዮሎጅና ባዮ-ስታትስቲክስ ትም/ክፍል ሀላፊ ረዳት ፕ/ር ደሴ አበባው ገልጸዋል፡፡
* * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * *
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ህዳር03/2013 ዓ.ም







