በስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን /JEG/ ስልጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሰው ሃብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የደሞዝ ስኬል አፈጻጸም እና የስራ ተውውቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከጥር 08-09/2012 ዓ.ም በጃንተከል ሆቴል እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው የሰው ሃብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አስማማው ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሰረት ካሴ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን /JEG/ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸው፣ ነገር ግን በተካሄደው ድልድል በሚፈጠሩ ክፍተቶች የማረምና የማስተካከል ስራዎች መሰራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በስልጠናው ከ35 በላይ የፋይናንስና የሰው ሃብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ተሳታፊ ሲሆኑ ዋና ዓላማውም ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በማረም ቀጣይ በሚደረገው የምደባ ደብዳቤ አጻጻፍና የደሞዝ ስኬል በተመለከተ በእውቀት ላይ ተመስርቶ በጥንቃቄ እንዲሰራ ለማድረግ እንደሆነ በስልጠናው መግቢያ ላይ ተገልጿል፡፡
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



