በስነ-አእምሮ ጤና ኢፒዲሚዮሎጅ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመክፈት የውጭ ገምጋሚዎችን ያሳተፈ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት አውደጥናት /External Curriculum Workshop/ ተካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ የስነ አእምሮ ትም/ክፍል ከህብረተሰብ ጤና ተቋም ጋር በመተባበር በስነ-አእምሮ ጤና ኢፒዲሚዮሎጅ የሶስተኛ ዲግሪ ለመጀመር የውጭ ገምጋሚዎችን ያሳተፈ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት አውደጥናት/ External Curriculum Workshop/ የኮሌጁ አመራሮች፣ ምሁራንና የውጭ ገምጋሚዎች በተገኙበት ግንቦት 5 /2013 ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ አካሄደ፡፡

በአውደ ጥናቱ በስነ-አእምሮ ጤና ኢፒዲሚዮሎጅ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመክፈት የተዘጋጀው የስርአተ ትምህርት ንድፍ/ድራፍት/ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ የጤናና ስነ ባህርይ ሳይንስ ትም/ክፍል መምህር በሆኑት በዶ/ር ተላከ አዛለ ለውጭ ገምጋሚዎች የቀረበ ሲሆን ፣ ከተቋሙ ውጭ የተጋበዙ ኤክስፐርቶችም በስርአተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ ያላቸውን እይታ የሚገልጹ የግምገማ ጽሁፎችን አቅርበዋል፤ ሊካተቱ የሚገባቸው ተጨማሪ መሰረታዊ ነጥቦችም በምሁራኑ ተነስተዋል፡፡
ከተቋሙ ውጭ ያሉ በሙያውና በምርምር ስራዎች ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸውን ምሁራን ሀሳብ ለማካተት ይህ የውጭ የስርአተ ትምህርት አውደጥናት/External Workshop/ መዘጋጀቱን የስነ አእምሮ ትም/ክፍል ኃላፊ አቶ ጎሹ ኔንቆ ገልጸዋል፡፡ አቶ ጎሹ አያይዘውም ለአውጥናቱ መካሄድ አስተዋጽኦ ላደረጉ የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም አስተባባሪዎች፣ የካሪኩለም ዝግጅት ኮሚቴና የስነ አእምሮ ትም/ክፍል ስታፍ አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከዚህ በፊት የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ያሳተፈ የውስጥ የካሪኩለም አውደጥናት በግቢው መካሄዱ ይታወሳል፡፡
በስነ-አእምሮ ጤና ኢፒዲሚዮሎጅ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመክፈት የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አውደጥናት ተካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ የስነ አእምሮ ትም/ክፍል ከህብረተሰብ ጤና ተቋም ጋር በመተባበር በስነ-አእምሮ ጤና ኢፒዲሚዮሎጅ የሶስተኛ ዲግሪ ለመጀመር የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አውደጥናት ህዳር 18/2013 ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ አካሂዷል፡፡
በአውደ ጥናቱ በስነ-አእምሮ ጤና ኢፒዲሚዮሎጅ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመክፈት የተዘጋጀው የስርአተ ትምህርት ንድፍ/ድራፍት/ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ የጤናና ስነ ባህርይ ሳይንስ ትም/ክፍል መምህር በዶ/ር ተላከ አዛለ ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን ፣ በቀረበው የስርአተ ትምህርቱ ንድፍ ላይ ዉይይት ተደርጓል፣ ሊካተቱ የሚገባቸው ተጨማሪ መሰረታዊ ነጥቦችም በምሁራን ተነስተዋል፡፡
በሙያውና በምርምር ስራዎች ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸውን ምሁራን ሀሳብ ለማካተት ይህ የውስጥ አውደጥናት/Internal Workshop/ በስታፍ ደረጃ መዘጋጀቱን የገለጹት ዶ/ር ተላከ፣ በቀጣይም የውጭ አካለትን ያካተተ አውደጥናት/External Workshop/ ይካሄዳል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ተላከ አዛለ አያይዘው እንዳብራሩትም የስነ አእምሮ ጤና አለምአቀፍ ትኩረት ቢሰጠውም በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች የስነ-አእምሮ ጤና አገልግሎትም ሆነ ምርምር የተስፋፋ አይደለም፡፡ ስለሆነም በዩኒቨርሲቲያችን በዚህ መስክ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት መከፈቱ የስነ አእምሮ ጤና አገልግሎትን በማሻሻል የህብረተሰቡን የጤና ችግር ለመቅረፍ እንዲሁም ህብረተሰቡ ያለው የስነ አእምሮ ጤና ግንዛቤ ለማሳደግ እንደሚረዳ ይታመናል፡፡
* * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * *
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና አለምዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ህዳር 18/2013 ዓ.ም







