በቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ ተዘጋጀ
የቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክ በደቡብ ወሎ ዞን በስድስት ወረዳዎች (ቦረና ሳይንት፣ መ/ሳይንት፣ ለጋምቦ፣ መቅደላና ተንታ) መካከል የሚገኝ ፓርክ ነው፡፡ ይህ ፓርክ በ2001 ዓ.ም የፓርክነት ደረጃን እንዳገኘ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ጠቅላላ ስፋቱም 15262 ሄ/ር ሲሆን በከፍታው ደግሞ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ቦታዎች ማለትም ከሰሜን ብሄራዊ ፓርክና ከባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ቀጥሎ በ3ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል፡፡
ብሄራዊ ፓርኩ በርካታ ቀልብን የሚስቡ ህይወታዊና ሌሎች የተፈጥሯዊ ቅርሶች እንዲሁም የባህል እሴቶች የሚንጸባረቁበት ስለሆነ የቱሪስት መዳረሻ የመሆን አቅም ያለው ፓርክ ነው፡፡ በተለይ ከተፈጧዊ ቅርሶችና መስህቦች መካከል የተመልካችን ቀልብ በቀላሉ የሚይዝ ውብና ማራኪ የተፈጥሮ ደን (የከፍተኛ ቦታዎች እጽዋት) መገኛ፣ አስገራሚና አስደናቂ የተፈጥሮ ዋሻዎች እንዲሁም የተፈጥሮ ፏፏቴዎችና ጅረቶች ያሉበት ከመሆኑም በተጨማሪ የተለያዩ ብርቅየ የዱር እንሰሳትት ለአብነት ያህል ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዥንጀሮ፣ ሚኒሊክ ዱኩላ፣ የስታርክ ጥንቸል እና የመሳሰሉት በውጡ ይገኙበታል፡፡
እንደሚታወቀው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል የሚገኙ ፓርኮችና ጥብቅ ደኖች ህልውናቸው በዘላቂነት ኢንዲጠበቅ በማድረግ በኩል በሀገር አቀፍና በተቋም ደረጃ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክ ያሉ የተፈጥሮ ገጸ በረከቶች በአግባቡ ኢንዲያዙና ክብካቤ እንዲደረግላቸው ለማስቻል፣ ዩኒቨርሲቲው ከመቅላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአካባቢው ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችና የዘርፉ ሙያተኞች ጋር የጋራ የምክክር መድርክ ከሰኔ 16-17/2011 ዓ.ም በመካነ ሰላም ከተማ አካሂዷል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕረዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔ፣ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ወንድየ አድማሱ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ፈንታው፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ሙህራንና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡
በዕለቱ የቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክ ችግርቹና ጸጋወቹ በስፋት ተዳሰዋል፤ ሌሎች ብሄራዊ ፓርኮች ያላቸው ተሞክሮ (በተለይም የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ) ቀርቧል፤ ህገ ወጥ አደን መንስኤውና የሚያስከትለው ጉዳት ተተንትኗል፤ ብሄራዊ ፓርኮች ሊኖራቸው የሚችል ከባቢያዊ ፋይዳና ተያያዥ ነጥቦች ተነስተው በስፋት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ተያይዞም በአባይ ሸሎቆ (ወሎና ጎጃምን በሚያዋስነው) ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ መዐድኖችና ንጥረ ነገሮች (መዓድናማ ዓለቶች)፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሙህራን በኩል ትኩተርት ተሰጥቶ ለምርምር እንዲውሉ ለማስቻል ናሙና ተወስዶ በምርምር ላይ እንደሚገኙ በውይይቱ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ይበጃሉ የተባሉ ሀሳቦች ላይ በመግባባትና የወደፊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡