በወቅታዊ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የመማር ማስተማር ሂደት ዛሬ ጀመረ
በኮቪድ-19 ምከንያት በሀገሪቱ ከፍተኛ የትም/ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቱ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ አድረጎ ታህሳስ 5/2013 ዓ.ም የመጀመሪያውን መደበኛ የመማር ማስተማር ቀን / Day one Class one /በይፋ እንደሚጀምር መግለጹ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም ዛሬ ማለትም ታህሳስ 5/2013 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች መደበኛ የመማር ማስተማርያ ሂደቱ መከናወን ጀምሯል፡፡ የመስክ የቡድን ስልጠና / Team Training Program / ፕሮግራም ላይ የሚሳተፉ የህምናና የጤና ተማሪዎችም በመስክ ፕሮግራም የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች መሰረት ያደረገ ተግባራዊ ትምህርት ለመውሰድ በዛሬው እለት በሳይንስ አምባ አዳራሽ አጠቃላይ ‘ኦረንቴሽን’ በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡ በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎችም የማስተማር ሂደቱ ተግባራዊ መሆኑን በየግቢው በመንቀሳቀስ እያረጋገጡ ነው፡፡
ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት በሰላም ተመለሳችሁ!
*****************************************************************
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ታህሳስ 5/2013 ዓ.ም







