በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎችና ጎረቤት ሃገራት ለሚገኙ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በየዓመቱ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ በማድረግ እያስተማረ ይገኛል፡፡

እነዚህ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የትምህርት ዕድል ሰጥቶ የሚያስተምራቸው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው ባሻገር የተለያዩ የህዎት ክህሎት ስልጠናዎችን እወሰዱ ይገኛሉ፡፡

የካቲት13/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ሳምንት የሚቆይ ስልጠና በማራኪ ግቢ 45 ለሚሆኑ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ’’አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መዋቅሮች እንዲሁም በአካል ጉዳተኛች አካቶ ልማት በሚሉ ሁለት ይዘቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ይህ ስልጠና በተመሳሳይ በቀጣዩ የክረምት ወራት በመሪነት፣ በህግና በሌሎች ዘርፎች ስልጠናው እንደሚቀጥል ማወቅ ተችሏል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓለማም ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደየመጡበት አካባቢ ሲመለሱ ይህን እድል ላላገኙ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች መስራት እንደሚችሉና መብታቸውንም ማወቅ እንደሚገባቸው ሞዴል በመሆን የማስተማር ሥራ እንዲሰሩ ለማደረግ ነው፡፡
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



