በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የተዘጋጀ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሽኝት መርሃ – ግብር. ተካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተዘጋጀ 12ኛ ክፍልን አጠናቀው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሽኝት መርሀ – ግብር ሰኔ19/2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው እንግዳ መቀበያ ሆቴል ተካሂዷል።
በመርሀ -ግብሩ ዶ/ር ካሣሁን ተገኘ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት፣ ዶ/ር መሠረት ካሴ የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንት፣ አቶ እንግዳው አቡሃይ የማህበረስብ ትምህርት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ የተማሪ ወላጆች እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

አቶ ወንድይራድ ጌጡ የማህበረሰብ የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የእንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ዶ/ር መሠረት ካሴ መርሃ – ግብሩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀምሩ ሲሆን ፣ አያይዘውም ተማሪዎቹ በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ዓላማን አንግበው በመማርና የመጀመሪያ ዓመት ውጤታቸውን በማስጠበቅ እንዲሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ሴቶች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው የ2012 ዓ.ም ፈተናን ልዩ የሚያደርገው መሆኑን አንስተዋል።
በመቀጠልም በትምህርት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ እንግዳው አቡሃይ የተማሪዎችን የውጤት ትንተና የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቧል።
በዝግጅቱ የትምህርት ቤቱ የተማሪ ወላጅ ተወካዮች፣ መምህራንና ነባር ተማሪዎች ምክር አዘል አስተያየት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሣሁን ተገኘ የዕለት ተለት እቅድ በማውጣት እና ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም ውጤታቸውን እንዲያስጥብቁ ባስተላለፉት የመዝጊያ ንግግር ፕሮግራሙ ተጠናቋል።




