በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በሕዝብ ግንኙነት ሥራ ላይ እየሰራ ያለውን ልምዱን አካፈለ
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች የሕዝብ ግንኙነት አሰራር ምን ይመስላል በሚል

ከየካቲት 21 እስከ 22/2012 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው ውይይት ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ልምዱን እንዲያካፍል የተጋበዘ ሲሆን የቅንጅት አሰራሮችን፣ የሚዲያ አጠቃቀምን፣ ችግር ፈች አሰራሮችንና ከተማሪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ሪፖርት አቅርቧል።

በሪፖርቱ ለቀረበው ጥያቄም ምላሽ ተሰጥቷል። በመጨርሻም በጎንደር ዩኒቨርሲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የኮምዩኒኬሽ አሰራሩ የተሻለ እንደሆነ ከተለየዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



