በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ስልጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎማቲክስ ፋኩሊቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ክፍል ያዘጋጀው ስልጠና ከየካቲት 18/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና በዓፄ ቴዎድሮስ ግቢ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

እየተካሄደ ያለው ስልጠና ’’Improving Social Media usage Among Amhara Region Government Communication and public Relation Officers in case of three Gondar Zones (Central, North and West’’ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊዎች ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ከሰሜን ጎንደርና ከምዕራብ ጎንደር የተውጣጡ የሕዝብ ግንኙነት ባከሙያዎች ሲሆኑ የሥልጠናው ዋና ዓለማ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ለማሻሻልና በአገራዊ ልማት ላይ ያለውን ተግዳሮት ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

በስልጠናው በኢንፎርማቲክስ ፋኩሊቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ፈድሉ ኑረሁሴን የእንኳን ደህና መጣቸሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የፋኩሊቲው ዲን አቶ ቴዎድሮስ ዓለሙ የመክፈቻንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ሰልጣኞቹን እንኳን ወደ ሰላሙ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ’’ወቅቱ የማህበራዊ ሚዲያ አገርንና ህዝብን እየጎዳ ያለበት ጊዜ በመሆኑን እንደ ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ ስልጠናውን በሚገባ በመከታተል ሚዲያውን ለአገራዊ የገፅታ ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል’’፡፡
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



