በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ፣ በነጥብ ድልድል ስርዓት መሰረት ከደረጃ 9 አስከ ደረጃ 18 የተመደቡ ሰራተኞች ከከፍተኛ አመራሩ ጋር በነበረው ውይይት ያወጡት የአቋም መግለጫ፦
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ፣ በነጥብ ድልድል ስርዓት መሰረት ከደረጃ 9 አስከ ደረጃ
18 የተመደቡ ሰራተኞች የካቲት 14/2012 ዓ.ም ከከፍተኛ አመራሩ ጋር በነበረው ውይይት ያወጡት የአቋም መግለጫ፦
1. የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “የሰላሙ ዩኒቨርሲቲ” የሚለውን መለያ ስም ከምንግዜውም በተሻለ እና በላቀ ሁኔታ
አጠንክረን በማስቀጠል የመማር ማስተማር፣ የምርምር፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና የቴክኖሎጅ ሽግግር ስራው
ያለምንም እንከን በላቀና በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲከወን እኩይ እና አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸውን በንቃት በመከታተል
የዩኒቨርስቲያችን የሰላም ፖሊስ እና የጸጥታ አስከባሪ ሆነን ለመቆም ቃል እንገባለን፡፡
2. በተመደብንበት የስራ ክፍል ኃላፊነታችንን በመወጣት በአጭር ጊዜ ፍሬያማና የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት፣ በታማኝነትና በቅንነት በመስራት ለውጭ እና ለውስጥ ደንበኞቻችንን ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
3. ዩኒቨርሲቲያችን የእኛ፣ የቤተሰቦቻችን፣ የአካባቢያችን ብሎም የሀገራችን ሀብት በመሆኑ፣ በተቋሙ ያለውን ሀብትና ንብረት እንደራሳችን አድርገን በማየት በአግባቡ በመያዝ እና በመጠበቅ ለተፈለገው አላማ ብቻ እንዲውል አጥብቀን እንሰራለን፡፡
4. በአሰራር ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ክፍተቶችንና ቅሬታዎችን የመንግስት የቅሬታ አፈታት ስርዓትን በመከተል ወቅታዊ ምላሽ እንዲያገኙ የድርሻችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡
5. በዩኒቨርሲቲያችን በነጥብ የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን መሰረት የሰራተኛ ምደባ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተከናውኖ ወደ ሰራተኛ ድልድል መገባቱን እያደነቅን፣ ከተቋሙ የስራ ስፋት እና እድገት አንፃር አንዳንድ የስራ መደቦች ደረጃቸው ዝቅ ብሎ በመምጣቱ፣ በስራ እንቅስቃሴዎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ መፍጠሩ አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ደረጃቸው ዝቅ ብሎ በመጡ የስራ መደቦች ላይ በጥናት የተደገፈ የደረጃ ከፍታ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጥያቄው እንዲቀርብ አበክረን እንጠይቃለን፡፡
“የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አንዳችን እንደ ሁላችን፣ ሁላችን እንደ አንዳችን በጋራ የመስራት ባህላችን እናሳድግ”
የካቲት 14/2012 ዓ.ም



