ተ/ፕሮፌሰር አማረ ታሪኩ አገር አቀፍ የወጣት ተመራማሪ ውድድር አሸነፉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ የ”ሂዩማን ኒትሪሽን” መምህር ተ/ፕሮፌሰር አማረ ታሪኩ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና አጠባበቅ ማህበር አመካኝነት በሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የምርምር ውድድር የአመቱ ምርጥ ወጣት የህብረተሰብ ጤና ተመራማሪ ተብለው ተመረጡ፡፡ በአ.አ ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በተካሄደው በዚህ የውድድርና የሽልማት ስነ-ስርዓት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና አጠባበቅ ማህበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ምትኬ ሞላና የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊወች ተገኝተዋል፡፡

ተ/ፕሮፌሰር አማረ ታሪኩ የ3ኛ ዲግሪ የ”ሂዩማን ኒትሪሽን”/ስነ-ምግብ/ተማሪ ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲው ግንባር ቀደም ተመራማሪ ከሚባሉት አንዱ ናቸው፡፡ በአካዳሚክና በማህበረሰብ አገልግሎት በርካታ ውጤታማ ስራዎችን በመስራታቸውና ከ60 በላይ የምርምር ህትመቶችን በታዋቂ ጆርናሎች በማሳተማቸው ውድድሩን ለማሸነፍ እንዳበቃቸው ተመራማሪው ተናግረዋል ፡፡

የህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ አካዳሚክ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስማማው አጥናፉ ተመራማሪው የምርምር ወድድሩን በማሸነፋቸው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማዕከል ሆኖ ለመመረጡ ጥሩ ማሳያ በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ስታፍ አባላትም የተ/ፕሮፌሰር አማረ ታሪኩን ፈለግ በመከተል የህ/ሰቡን የጤና ችግር ሊፈቱ የሚችሉ አገር አቀፍና አለም አቀፍ የምርምር ስራዎችን ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡



