አዲስ የግብርና ቴክኖሎጂ ማላመድ ተቻ
ለየጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳትና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቢሮ ጋር በመተባበር፣ ‘ኢሴንያ ፎኤቲዳ’ የተባለ አነስተኛ ነብሳት በመጠቀም፣ የዶሮ ምግብ ግብአቶችንና የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚችል አዲስ ቴክኖሎጂን ማላመድ ችለዋል፡፡

ኢሴንያ ፌኤቲዳ ከ580 – 710 ግ እምቅ ፕሮቲን፣ ሁሉንም አይነት ኢሚኖ አሲዶች፣ እጅግ በጣም ብዙ የላይዚንና ሎሎች ክምችቶችን ከመያዙም በላይ በፍጥነት መራባት በመቻሉና በሽታን በመቋቋም አቅሙ ከሌሌች አንስተኛ የመሬት ነፍሳቶች እንደሚለይ የፕሮጅክቱ አስተባባሪ ዶ/ር አብርሀም አየለ ገልጸዋል፡፡ አስተባባሪው አያይዘውም የፈጠራ ውጤቱ በዋናነት ለዶሮ ምግብ ተመራጭ ቢሆንም የአፈር ለምነትን በመጠበቅ በኩል አወንታዊ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር አብርሀም ከዩኒቨርሲቲው ባሻገር በዶሮ እርባታ የተሰማሩ የጎንደርና አካባባው የህብረተሰብ ክፍሎችን በቴክኖሎጅው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

በመሆኑም ቴክኖሎጅውን (ነብሳትን የማለመድና የማብዣ ጣቢያውን) ለሚለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ውስን ሙያተኞች ሙሉ በሙሉ ተረክበው እንዲያስቀጥሉት ማስቻልን ዓለማ ያደረገ የ አምስት ቀናቶች ስልጠና (ከግንቦት 10 -14/2012 ዓ.ም) መሰጠት ጀምሯል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በዶ/ር ጸጋው ፈንቴ ቀርቧል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጅ ሽግግርና ዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር ዶ/ር ውለታው መኩሪያ ስልጠናውን በግግር አስጀምረዋል፡፡

ስልጠናው እየተካሄደ የሚገኘው የወቅቱን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል፡፡
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



