አገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረት ውይይት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አባላትና ሌሎች ተማሪዎች አገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ”Zoom Meeting” ቀጥታ በመቀላቀል ለመሳተፍ የኮኔክሽን መቆራረጥ ችግር ቢያጋጥማቸውም ” ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መርሃ ግብር ሰኔ 3/2013 ዓ.ም በመረጃና ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የስልጠና ማዕከል ከ4፡00 ጀምሮ በተካሄደው አገራዊ ጉዳይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በሌላ በኩል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሁለት ቀናት ማለትም ከሰኔ 3-4/2013 ዓ.ም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዓለም አቀፍ የውሃ ህግ፣ ሉዓላዊነትና የግጭት አፈታት በሚል ርዕስ 9ኛውን አገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ጉባኤ እና 3ኛውን አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን በማስመልከት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡



