“ወል ኢትዮጵያ” የተሰኘ ሙዚቃዊ ድራማ ለተመልካች ቀረበ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል #ወል ኢትዮጵያ $የተሰኘ ሙዚቃዊ ድራማ ጥር 25/2010ዓ/ም ከቀኑ 12፡30 ጀምሮ ማራኪ ግቢ በቴአትር አዳራሽ ለተመልካች አቀረበ፡፡ በዕለቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ም/ ዲን አቶ አይሸሽም ተረፈ፣ የሶሾሎጂና ሶሻል ወርክ ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ታፈረ፣ የኮሌጁ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ኢብራሂም ዳምጠው፣ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል መምህራን፣ የሙዚቃ ትምህርት ክፍል መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
“ወል ኢትዮጵያ ሙዚቃዊ ድራማ” uመምህር ተመስገን አስራት የተደረሰና የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሙዚቃዊ ድራማው ወቅታዊ ፣ አስተማሪ፣ አዝናኝና ሀገራዊ የሆነውን የአለባበስ፣ የአመጋገብ፣ የአኗኗር፣ የአዘፋፈን፣ አብሮ መኖርና፣ አንድነትን የሚገልጽ፣ እንዲሁም ስለ ሀገር ፍቅር ጥልቅ መልእክትን የሚያስተላልፍ፣ ቴአትሩ በከፍተኛ ሁኔታ አዝናኝና አስተማሪ የሆነ፣ በአጭር ሰአት ሰፊ መልእክትን ለታዳሚው ያስጨበጠ/ያስገነዘበ ነበር፡፡
[widgetkit id=8287]
መምህር ምስጋናው አለሙ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፣# የቀረበው ቴአትር በዋናነት ለ3ኛ አመት የቴአትር ጥበባት ተማሪዎች ለኮርስ ማሟያነት የተሰራ ቢሆንም፣ ካለው ሀገራዊ ጭብጥ አንፃር ለሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቅርበናል፡፡ እንደ ትምህርት ክፍልም እንዲህ አይነት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ስራዎች በመስራት የድርሻችን እንወጣለን ብለን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፣ ወደፊትም በሀገራዊና ብሄራዊ በአላት ላይ የሚቀርቡ ትልልቅ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን$ ብለዋል፡፡
በቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት #የወል ኢትዮጵያ ሙዚቃዊ ድራማ $ደራሲና አዘጋጅ መምህር ተመስገን አስራት በሙዚቃዊ ድራማው ማስተላለፍ የተፈለገው ዋናው መልዕክት ህዝቡ ፍቅርን፣ መቻቻልን፣ አንድነትን፣ አብሮ መኖርን፣ አብሮ መብላትን፣ አብሮ መጠጣትን በእሴቱ ይዞት ጠብቆት የቆየ መሆኑንና በዚህ እሴት ደግሞ በአንድነት ሀገርን ተባብሮ ከማሳደግ አንፃር ያለውን ፋይዳ አጉልቶ ለማሳየት የተሞከረ ነው ብለዋል፡፡ መምህር ተመስገን በመጨረሻ የሙላለም ባህል ማዕከልን፣ የጎንደር ከተማ ባህል ማዕከልን፣ የዩኒቨርሲቲውን ባህል ማዕከል፣ ለሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህራንና የትምህርት ክፍሉን መምህራን አመስግነዋል፡፡
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የመዝጊያ ንግግር ሲያደርጉ፣ #በአቀረባችሁት ቴአትር በጣም ኮርቻለሁ! ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ ህይወታችንን፣ ኑሮአችንን የሚገልፅ ነው፤ እየሰራችሁት ያለው ስራ በጣም ተስፋ ሰጪና ዩኒቨርሲቲያችን በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚችልና ብዙ የጥበብ ሰዎችን እንደሚያፈራ ተስፋ አደርጋለሁ$ ብለዋል፡፡አያይዘውም #ሀገራችን የታሪክ፣ የጀግና፣ የአብሮነት ፣የመቻቻል፣የፍቅር ሀገር የሆነች ትልቅ ሀገር ናት፡፡ በጋራ የኖርን ህዝቦች ነን ፤ስለዚህ በጋራ አብረን መኖር መቻል አለብን፤ ዘረኝነት የሚጠቅም አይደለም ፤ድህነትንም ሆነ ሌሎችንም ማሸነፍ የምንችለው አንድ ስንሆን ነው፡፡$ ብለዋል፡፡በመጨረሻም አዘጋጆችን፣ በቴአትሩ ላይ የተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች፣ ኮሌጁን፣ የትምህርት ክፍሎችንና ሌሎች ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነው ፕሮግራሙን ዘግተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- የሽመቤት ኃይሉ
ከህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



