“ውጤታማ የአሰለጣጠን ዘዴ” በሚል ርዕስ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት “ውጤታማ የአሰለጣጠን ዘዴ” በሚል ርዕስ ዛሬ ማለትም መጋቢት 21/2013 ዓ.ም የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በአፄ ቴወድሮስ ግቢ T12 አዳራሽ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናውም ለ6 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚሰጠውም በጎንደር ዙሪያ በተመረጡ 6 ወረዳዎች ማለትም አይከል ከተማ አስተዳደር፣ ጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ ደንቢያ ወረዳ፣ ገንዳውሃ ወረዳ፣ ላይ አርማጭሆ ወረዳ እና ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ለተውጣጡ የኳስ ስፖርት (የእጅ ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ ና እግር ኳስ) አሰልጣኞችና የስፖርት ሳይንስ መምህራን ነው ፡፡

“በማንኛውም ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ተከታታይ ስልጠና በመውሰድ ራስን ማብቃት ተገቢ ነው” ሲሉ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ ተናግረዋል፡፡ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት የትምህርት ክፍሉ መምህራን አቶ መኳንንት ሽካባው (የስልጠናው ዋና አስተባባሪ)፣ ዶ/ር ሙሃመድ እድሪስ፣ ዶ/ር ኤፍሬም ታምራት እና አቶ ዩሀንስ አንዳርጋቸው ሲሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ በዞናችን የሚሰጡ የስፖርት የስልጠና ዘዴ ወጥነት እንዲኖራቸውና ዘመኑን የዋጀ የስልጠና ሂደት በመከተል በስፖርቱ ውጤታማ መሆን ነው ሲሉ የስልጠናው ዋና አስተባባሪ አቶ መኳንንት ሽካባው ተናግረዋል፡፡




