“ዘመናዊ የፍየል እርባታ ዘዴዎችና እርባታውን ለማዘመን የሚያስችሉ ስልቶች” በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ከምዕራብ በለሳ እና ከኪንፋዝ በገላ ወረዳዎች ለተመረጡ አርብቶ-አደሮች ስለዘመናዊ የፍየል እርባታ ዘዴዎችና እርባታውን ለማዘመን የሚያስችሉ ስልቶች በሚል ርዕሰ ጉዳይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በአርባያ ከተማ ታህሳስ 10 እና 11 ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው የተዘጋጀው ላለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ በተደረገ የፍየልና የበግ እርባታ ሁኔታ፤ ገበያና ዝርያ ማሻሻል ላይ ያተኮረ የምርምር ስራ በመሰራቱ ምክንያት የተገኘውን የምርምር ውጤት መነሻ በማድረግ እንደሆነ የስልጠናው አስተባበሪና የእንስሳት ሳይንስት ምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሀብታሙ አያሌ…
See More







