
የመቅዳላ አምባ ዩኒቨርሰቲ ላሞችን ተረከበ
የጎንደር ዩኒቨረሰቲ የእንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ በሚያከናውናቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች ክዚህ በፊት ለአካል ጉዳተኞችና ለተደራጁ ስራ አጥ ወጣቶች የወተት ላሞችን መስጠቱና መሰል እገዛዎችን ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ በምርምር ስራዎች ከፍተኛ ልምድ ያለው አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨረሲቲ በቅርቡ ለተቋቋመው ለመቅደላ አምባ ዩኒቨረሲቲ ጤናቸው የተጠበቀና ለወተት ምርት የሚሆኑ የውጭ ዝርያ ያላቸው ላሞችን (3 ያልወለዱ ጊደሮችና 2 የወለዱ ላሞችን) በተመጣጣኝ ዋጋ አስረክቧል፡፡

ኮሌጁ ሞዴል የሆነ ፋርም እንዳለውና በዚህ ፋርም ተማሪዎችን በተግባር ከማስተማር በተጨማሪ የወተት ላሞች እርባታ፣ የዶሮ እርባታ፣ የማድለብና የመሳሰሉ ስራዎች እደሚከናወኑበትም ከኮሌጁ ዲን ከዶ/ር ሽመልስ ዳኛው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
