የመግቢያ ቀናትን ማራዘም
ለጎንደር ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ
የ2012 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀናት ለነባር ተማሪዎች መስከረም 22 እና 23/2012ዓም እና ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች መስከረም 28 እና 29/2012ዓ.ም እንደሆነ ማሳወቃችን ይታወሳል።
ነገር ግን በወቅታዊ ችግሮች ምክንያት የመግቢያ ቀናትን ማራዘም አስፈልጓል።
ስለሆነም የነባር ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ወደ መስከረም 29 እና 30/2012ዓ.ም እንዲሁም የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ወደ ጥቅምት 6 እና 7 ቀን 2012ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።
የጎንደር ዮኒቨርሲቲ



