የስትራቴጅክ እቅድን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የስትራቴጅክ እቅድን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከግንቦት 3-6/2013 ዓ.ም በጎንደር ኦሎምፒክ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲያችን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከእያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምን እንደሚጠበቅ በማሳሰብ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የስልጠናውን ሀሳብ ከማፍለቅ ጀምሮ እስካሁን በሃላፊነት እያስተባበረ ለሚገኘው ለእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት የ10 አመቱን ስትራቴጅክ እቅድ አዘጋጅቶና አፀድቆ ወደሁሉም ፈፃሚ አካላት በማውረድ የካስኬዲንግ ስራ እንዲሰራ ለማድረግ በመካከለኛ እርከን ላይ ለሚገኙ የኮሌጅ ዲኖች ፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም የአካዳሚክ ዳይሬክተሮች ፣ የእቅድ ዝግጅትና የካስኬድ ቲም አባላት በዚህ በመጀመሪያው ዙር ስልጠና እየተሳተፉ እንደሚገኙ የእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው ነበሩ ገልጸዋል፡፡



