የስነ-ደዌ/ፓቶሎጅ/ ትም/ክፍል የማስፋፊያ ህንፃ ተጠናቆ ተመረቀ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል የፓቶሎጅ/ስነ-ደዌ/ ትም/ክፍል የማስፋፊያ ህንጻ ግንባታ ተጠናቆ ጥቅምት 21/2013 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ በህንጻ ምረቃ ስነ-ስርዓቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በርካታ የተጀመሩ ህንጻዎችን ግንባታ ለማስጨረስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ያሉትን አመራሮችና ባለሙያዎች የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አመስግነዋል፣ በቀጣይም ተመሳሳይ የማስፋፊ ህንጻዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ግንባታው ተጠናቆ በዕለቱ የተመረቀው G+1 ህንጻ ከስሩ ቤዝመንት ያለው ሲሆን ለግንባታው 4.5 ሚሊዮን ብር ያህል ስራ ላይ መዋሉን የፓቶሎጅ/ስነ-ደዌ/ትም/ክፍል ሃላፊ ዶ/ር ጥሩዘር በቀለ ተናግረዋል፡፡ ሕንጻው የተገነባው በዮኒቨርቲው ባለሙያዎች ሲሆን ይህ የማስፋፊያ ህንጻም ለተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመማር ማተማር፣ ለምርምርና ለህክምና መስጫ አገልግሎት እንደሚውል የገለጹት ዶ/ር ጥሩዘር፣ የግንባታውን ሂደት ፍጻሜ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን አመራሮች፣ የግዥ እና የጥገና ባለሙያዎች እንዲሁም የትም/ክፍሉ አባላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ለእነዚህ አካላትም በዕለቱ የማበረታቻ ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ********************************************************
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት21/2013 ዓ.ም






