የሶፍትዌር ስልጠና ለውሃ ልማት ጽ/ቤት ባለሙያዎች ተሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በሀይድሮሊክና ውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት ለምእራብ ጎንደርና በዙሪያው ለሚገኙ የወረዳ ውሃ ልማት ጽ/ቤት ባለሙያዎች የሶፍት ዌር ስልጠና ከግንቦት 18-21/2013 ዓ.ም በአጼ ፋሲል ግቢ ተሰጠ ፡
፡የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የምርምር፣ ህብረተሰብ አገልግሎትና የቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሀም ባየህ መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት የትምህርት ክፍሉ መምህራን ናቸው፡፡

የተለያዩ የሶፍት ዌር ፕሮግራሞች በመጠቀም የተሻለ መረጃ ለማቅረብ የውሃ ተፋሰስ አካላትን የልየታ ስራ መስራት፤ ለመስኖ ስራ ግብአት የሚሆን የውሃ ፍላጎት መወሰን፤ ለተለያዩ ተግባራት የሚውሉ የሃይድሮሌጅካል ሞዴሎችን ማበልጸግ፤ ከተሞች አካባቢ የሚታየውን የዝናብ ፍሳሽ አወጋገድ ስርአት መቅረፅና መተንተን እንዲሁም ግድብ ውስጥ የሚታየውን የደለል ክምችት ማሳዎቅና የመፍትሄ ሃሳብ የመጠቆም ስራ ለመስራት ታስቦ ይህ ስልጠና እንደተዘጋጀ የሀይድሮሊክና ውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና የስልጠናው ዋና አስተባባሪ አቶ ዓለሙ ተዘራ ገልጸዋል፡፡



