የቢሮ መገልገያዎችን ብልሽት በመለየት ሪፖርት የሚያደርግ ሲስተም ለመተግበር ስልጠና ተሰጠ፡፡
ዩኦጂ ቲኬት(UoG Tiket) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መረጃና ግንኙነት ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ስር በሚገኘው ሶፍትዌር ክፍል ተሰርተው ለአገልግሎት ዝግጁ ከሆኑት የሶፍትዌር/ሲስተም ፕሮጀከረቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም ሲስተሙን ስኬታማ በሆነ መልኩ አገልግሎት ላይ ለማዋል ያመች ዘንድ ለሚመለከታቸው ሙያተኞች (በዋናነት ለጽሀፊዎች) ዛሬ ግንቦት 10/2013 ዓ.ም የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ዩኦጂ ቲኬት – የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ክፍሎች በየጊዜው የሚጋጥማቸውን የቢሮ መገልገያዎችና የኤሌክትሮኖኪስ ውጤቶች እንከን በመለየት በፍጥነት ለዩኒቨርሰቲው አገልግሎትና ጥገና ክፍል መልዕክት ማስተላለፍ የሚችል ሲስተም ነው፡፡
ይህን የተመለከተ ስልጠና ከዚህ በፊት ለመረጃና ግንኙነት ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ጥገና ክፍል መሰጠቱን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡



