የተማሪዎችን ቅበላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ የዮኒቨርሲቲው አመራር ውይይት አደረገ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተማሪችን ቅበላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ግምገማዊ ውይይት በማራኪ ግቢ አልሙንየም ህንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ መስከረም 21/2013 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡

ውይይቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሰጠውን ወቅታዊ አቅጣጫ መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲአችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን የተመራ ነበር፡፡ ውይይቱ በተለይም የተማሪ ቅበላው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይኖረው መወሰድ ስላለበቻው ቅድመ ጥንቃቄዎች መፍትሄ ለማበጀት፤ እንዲሁም በሽታው ከተማሪዎች ሰለምና ደህንነት ጋር ሊኖረው የሚችለውን ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ግንኙነት ከወዲሁ በመገመትና ለችግሩ የላቀ ትኩረት ለመስጠት የተደረገ ነው፡፡ በተጨማሪም ጤናን መሰረት ያደረገ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት በዩኒቨርሲቲው ለማስፈን አመራሩ ውይይቱን አድርጓል፡፡

ሁሉም አልግሎቶች ለተማሪዎች ዝግጁ ሁነው እየጠበቁ እንደሚገኙ በመድረኩ የተገፀ ሲሆን ለተማሪዎች ቅበላና ከዚሁ ጋር ተያያዥ የሆኑ የስራ እንቅስቃሴዎችን የሚከታተሉ የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ውይይቱ ተጠናቋል፡፡



