የቴክኖሎጅ ስልጠና ለወጣቶች እየተሰጠ ነው
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመረጃና ግንኙነት ዳይሬክቶሬትና የጆርናሊዝም ትምህርት ክፍል ከአሜሪካ ኢምባሲ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያና የአሜሪካ ወጣቶች በባህል፣በታሪክና በመገናኛ ዘዴዎች ላይ የልምድ ልውውጥ በማድረግ ሥራ ፈጣሪና አገር ወዳድ እንዲሆኑ ለማስቻል ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ሀምሌ 10/2011 ዓ.ም በማራኪ ግቢ በጆርናሊዝም ትምህርት ክፍል የኮምፒዩተር ቤተሙከራ ለ3 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና ለ15 ተማሪዎች እየተሰጠ ሲሆን፣ ሰልጣኞቹ በጎንደር ከተማ ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከቆዩ ተማሪዎች የተመለመሉ ናቸው፡፡
ሥልጠናው እየተሰጠ የሚገኝባቸው ዘርፎች፣በሚዲያ ሥነምግባር፣ በሚዲያና በዶክሜንተሪ ፊልም አዘገጃጀት መሆኑን በመረጃና ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ሲኒየር የኔትወርክ አድሚኒስትሬተርና የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ እሱያውቃል ሲሳይ ገልጸዋል፡፡
ከ30 ዓመት በላይ ነዋሪነታቸውን በአሜ ሪካ ሃገር ሲያትል ላይ ያደረጉና ከ19 ዓመታት በፊት ’’Ethio-youth’’ የቴሌቪዥን ሚዲያ መስራች የሆኑት አቶ አሳየ አቡኔ የዚህ ፕሮግራም አስተባባሪ ሲሆኑ፣ በአሜሪካ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሃገራቸውን ባህል የማወቅ ችግር እየገጠማቸው በመሆኑ የሁለቱን ሃገራት ወጣቶች በማገናኘት የመረጃ ግንኙነት ለውውጥና የዕውቀት ሽግግር እንዲያደረጉ የሚያስችል የስልጠና ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል፡፡