የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ለተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል የኦዲት ባህል ከአንድ መስሪያ ቤት አንፃር (Audit Culture in the public sector) በሚል ርዕስ ለተመራቂ ተማሪዎች ሰኔ 7/2011ዓ/ም ማራኪ አልሙኒዬም አዳራሽ ስልጠና ሰጠ፡፡
የኦዲት ባህል ከመስሪያ ቤቶች አንፃር ምን እንደሚመስል ያለውን አሰራር ግንዛቤ ለመፍጠር፣ በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ያለውን ልምድ ለተመራቂ ተማሪዎች እውቅና ለመፍጠር ፣ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ያለውን በተግባር ከሚሰራው ጋር በማቀናጀት የወደፊት የስራ መስካቸውን ለመለየት እንደሚረዳ፣ ኢትዮጵያ የምትከተለውን የኦዲት ስታንዳርድ በተጨባጭ እየተሰራ ከሚገኘው ልምድ ጋር በማያያዝ እና አሰራሮችን ለማሻሻል አላማ ያደረገ ስልጠና እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ስልጠናው ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት በተገኙ በአቶ ስመኝ ካሴ እና በአቶ ደረጀ አስቻለ የተሰጠ ሲሆን፣ ከኦዲት አሰራር ጋር ተያያዥ የሆኑ ፅንሰ ሀሳቦች ትርጓሜ፣ ከኦዲት አስፈላጊነት፣ በክልሉ ተቋማት የሚሰሩም ሆነ ሌላው ማህበረሰብ በኦዲት ላያ ያለው አመለካከት ምን እንደሚመስል፣ ትክክለኛው ምን መሆን እንደነበረበት እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መነሻ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡
በቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸውል፡፡



