የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አገራዊ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ጉባዔ ከሰኔ 4-5/2013ዓ.ም አካሂዷል። ዩኒቨርሲቲያችን ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ የሠራቸውን የፈጠራ ውጤቶች ኢግዚቪሽኑ ላይ አቅርቧል።
በጉባዔው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲያችን ባለፉት 15 ወራት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደ ሐገር ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ በክቡር አቶ ደመቀ መኰንን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እጅ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷታል።

ተቋማችን ለዚህ ስኬት ላበቁት የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታላችን ኃኪሞች ጤና ባለሙያዎች እና አመራሮች፣ የተማሪዎች አገልግሎት እና ጥበቃና ደህንነት ጽ/ቤት ሠራተኛች፣ በተለያዩ መንገዶች እገዛቸው ያልተለየን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር፣ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የአብክመ ጤና ቢሮ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ በገንዘብ በቁሳቁስና በሃሳብ ሲያግዙን የነበሩ በአገር ውስጥና በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዩጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ በምርምርና ፈጠራ በመሳተፍ የተቸገሩ ወገኖቻችን በመርዳትና ስለወረርሽኙ ግንዛቤ በመፍጠር ሲሳተፉ የነበሩ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራንና ሠራተኞች፣ በአጠቃላይ ለዚህ ስኬት በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ከጎናችን ያልተለያችሁን አካላት ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
ፈጣሪ አገራችንና ሕዝቧን ከክፉ ይጠብቅልን!
ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት
===========================
ሰኔ 05/2013 ዓ.ም



