የእንስሳት ምርምር ስነ-ምግባር መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ በረቂቁ ላይ ውይይት ተደረገ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ባሻገር በጥናትና ምርምር፣ በቴክኖሎጅ ሽግግር፣ አዳዳሲ የሳይንስ ግኝቶችን በመፍጠር የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻልን እንደ ዋነኛ ዓላማ በማንገብ በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ ህብረሰተሰቡ በጤና፣ በትምህርት በግብርናና በመሳሰሉት አዳዲስ የሳይንስ ግኝቶችንና ቴክኖሎጅዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ከመስራትም ባሻገር እንስሳትን በአግባቡ በመንከባከብና ጤናቸውን በመጠበቅ ህብረሰሰቡ ከእንስሳት በተገቢ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በዩኒቨርሲቲው እንስሳት ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አያሌ የምርምር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
ዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ምርምር ስነ-ምግባርን በተመለከተ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነ መመሪያ በማርቀቅ ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ጋር ህዳር 5/2013 ዓ.ም አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ስነ-ምግባር ቦርድ ኃላፊ አቶ ንጉሴ ይግዛው (የስነ- አዕምሮ ባለሙያ) ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያቀረቡ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔ አውደ ጥናቱን በንግግር አስጀምርዋል፡፡
በአይነቱ ለየት ያለና በሀገራችን ፈር ቀዳጅ የሆነ የእንስሳት ምርምር ስነ ምግባር መመሪያ ጸድቆ ተግባራዊ ከሆነ፣ እንስሶች ልክ እንደ ሰው ሁሉ ርህራሄና ክብካቤ በተሞላበት መልኩ መብታቸው ተጠብቆ ለተፈለገው ወይም ለታሰበው ምርምር አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያው ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም በቶሎ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባ ፕ/ር መርሻ አሳስበዋል፡፡
******************
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ህዳር 22/2013ዓ.ም







