የኬ.ጂ ና የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተመረቁ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት (የበለጡ ት/ቤት) የአጸደ ህጻናት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና የመሰናዶ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ሀምሌ 6/2011 ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይና የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔ፣ የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንትና የማህበረሰብ ት/ቤቱ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መሰረት ካሴ፣ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የተማሪ ወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የምረቃ በዓሉን ታድመዋል፡፡
ወቅቱ የቴክኖሎጅ ዘመን እንደመሆኑ መጠን ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጅ ምጥቀጥ በማየት፣ መረዳትና በመመርመር አብረን እኩል ልንጓዝ ይገባል ያሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር መሰረት ካሴ ናቸው፡፡ ዶ/ር መሰረት በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው አያይዘውም ወላጆችና መምህራን ተቀናጅተው በመስራት ለሀገር የሚጠቅምና የእውቀት አድማስን የሚያሰፋ አስተምሮዎች ላይ ልጆቻችን እንዲያተኩሩ የጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይና የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔ በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው ከአጸደ ህጻናት እስከ ፍልስፍና ዶክትሬት (ከKG – PhD) የሚያሰለጥን ተቋም በመሆኑ ልዩ ደስታ እንደሚሰማቸው ገልጸዋል፡፡ ፕ/ር መርሻ አያይዘውም ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻችው የእኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የማህበረሰብ ት/ቤቱ በ2011 የትምህርት ዘመን 1425 (አንድ ሺ አራት መቶ ሀያ አምስት) ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደቻለ የገለጹት የት/ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ዘነበ መለሰ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሩ በትምህርት ዘመኑ የተከናወኑ አንኳር አንኳር ተግባራትን በሪፖርት መልክ ያቀውረቡ ሲሆን ለወደፊት ይበጃሉ ያሏቸውንም ምክረ- ሀሳቦች ጠቁመዋል፡፡
በእለቱ ሀገራዊ፣ አስተማሪነት ይዘት ያላቸውና ታዳሚዎችን ያዝናኑ የተለያዩ ስነ- ግጥሞች፣ መነባነቦች፣ ሽለላዎችና ዘፈኖች በትምህርት ቤቱ ታዳጊዎች ቀርበዋል፡፡
በተጨማሪም በእለቱ ‘ቱርፋት’ የተሰኘ በትምርት ቤቱ ተማሪዎች በተለይም በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተቋቋመ በጎ አድራጎት ማህበርም በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን በጎ ተግባራት በሪፖርት መለክ አቅርቧል፡፡ይህም በጎ ተግባር ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ለማስቻል ፈቃደኛ ለሆኑ የት/ቤቱ ተማሪዎች ርክክብ ተደርጓል፡፡
በትምህርት ዘመኑ አብላጫ ውጤት ላስመዘገቡ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች፣ ልዩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የትምህርት ቤቱ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ከት/ት ቤቱ ጋር አብረው ለሰሩ አጋር አካላት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ልዩ እንግዶች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡