የኮረና ወረርሽኝን ይበልጥ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ውይይት ከኃይማኖት አባቶች ጋር እየተደረገ ነው
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የሀገር ውጪ ድርጅቶች ጋር እንደሚሰራ
ይታወቃል፡፡ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በአጋርነት ከሚሰሩ ድርጅቶች መካከል ስኮፕ (SCOPE) የተሰኘው ድርጅት አንዱ ነው፡፡ ይህ ድርጅት በእናቶችና ህጻናት ጤና፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ፣ በእናቶች ጤና አገልግሎትና በመሳሰሉት የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ እየሰራ ይገኛል፡፡
ስለሆነም ድርጅቱ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲና ከጎንደር ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በጎንደር ከተማ ለሚገኙ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ለወንጌል መምህራን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ይበልጥ ለመከላከል ብሎም ለመቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የጎንደር ከተማ ጤና ጥበቃ ሙያተኞች፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የጎንደር ከተማ የኮረና ወረርሽኝ መከላከል ኮሚቴ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በውይይቱ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ መርሀ – ግብሩ ነገ ታህሳስ 15/2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ከውይይቱ አስባባሪዎች ከዶ/ር ጌታሁን አስረስና ከአቶ ስመኘው ሀንዴቦ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
******************
ሀጋራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግኝኙነት ዳይሬክቶሬት
ታህሳስ 14/2013 ዓ.ም







