የጃፓንና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንኙነት በአዲስ መልክ ሊጠናከር ነው
የጃፓንና ኢትዮጵያ ግንኙነት ረዥም ጊዜ ታሪክ እንዳለው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ለአብነት ያክል እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1930ዎቹ ዓ.ም በዓፄ ኃ/ሥላሴ እና በወቅቱ የጃፓን መሪ የተጀመረው ግንኙነት በ195ዎቹ ወደተሻለ ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ ቀጥሎም የጃፓንና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በአካዳሚክ ዘርፉ አብረው መሥራት የጀመሩ ሲሆን በተለይም በወቅቱ ከጃፓን ወደ ኢትዮጵያ መጠው የነበሩ የልዑካን ቡድን ይዘዋቸው ከመጡት የጃፓውያኑን ተወዳጅ የዛፍ ችግኞች በቁጥር 30 የሚሆኑትን ወደ ጎንደር ይዘው መጥተዋል፡፡ የመጡት ቸግኞቹም በፋሲል ገንብና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተተከለው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት እየተዳከመ የመጠጣውን የጃፓንና የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ግንኙነት ለማጠናከር ነሓሴ 5/2011 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሰቲ እንግዳ ማረፊያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የከፍተኛ ሳይንስ ሚኒቴር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይንና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል፡፡
የጃፓን የልዑካን ቡድንም በውውይቱ ለመገኘት ከላሊበላ ጎንደር ለመብረር በደረጉት ሙከራ በአየር ጸባይ ምክንያት እንዳልተገኙ ፕ/ር አፈወርቅ ተናግረዋል፡፡ የልዑክን ቡድኑን ወክለው ባቀረቡት ጽሑፍም ጃፓን ከኢትዮጵያና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የነበራትን ግንኙነት አሳይተዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረበው ጽሑፍ በፕሬዚዳንቶቹ አስተያየት ተሰጥቶበት ግንኙነቱ በአካዳሚክ ዘርፍ፣ በባህል፣በታሪክ፣በማህበረሰብ አገልግሎትና በሌሎችም ዘርፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የማደማደሚያ ሃሳብ ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
ዘጋቢ፡- በላይ መስፍን
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

በመጨረሻም በቀረበው ጽሑፍ በፕሬዚዳንቶቹ አስተያየት ተሰጥቶበት ግንኙነቱ በአካዳሚክ ዘርፍ፣ በባህል፣በታሪክ፣በማህበረሰብ አገልግሎትና በሌሎችም ዘርፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የማደማደሚያ ሃሳብ ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
ዘጋቢ፡- በላይ መስፍን
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



