‹‹የገቢያ ትስስር ለእደ ጥበብ አምራቾች›› በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል ‹‹የገቢያ ትስስር ለእደ ጥበብ አምራቾች›› በሚል ርዕስ ለጎንደርና አዲስ ዘመን ከተማ የእደ ጥበብ አምራቾች፣ የገቢያና ንግድ ባለሙያዎች ዛሬ ሰኔ 4 እና 5 /2013ዓ/ም በማራኪ ግቢ አልሙኒየም ህንፃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ዶ/ር ዋሴ ጌታሁን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያስጀመሩ ሲሆን፣ የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ደምስ አላምረው ፕሮግራሙን አስመልክተው ቁልፍ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ብዙውን ጊዜ አምራቹ ማህበረሰብ እውቀትና ክህሎቱን ተጠቅሞ ቢያመርትም አምራች ሀይሉ ብዙ ተጠቃሚ ሲሆን አለመታየቱን አንስተው ይህም ከእውቀትና ክህሎት ክፍተት የመነጨ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ይህንን ክፍተት ለመሙላት አላማ ያደረገ የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና መሆኑን ዶ/ር ደምስ አክለው ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው በገቢያ ትስስር ምንነት፣ በስራ ፈጠራ፣ በእደ ጥበብ ምርቶችና በባለ ድርሻ አካላት ሚና ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ አባል መምህራን በመ/ር ሙሀመድ ሰኢድ፣ በመ/ር ሉባባ ሸምሱና በዶ/ር ሙሉጌታ ነጋሽ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡




