የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስምንት የተለያዩ የጤና “ኢንፎርማቲክስ” ሞጅዩሎችን አዘጋጅቶ አስመረቀ
የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ “ሄልዝ ኢንፎርማቲክስ ዲፓርትመንት” ደረጃቸውን የጠበቁ ስምንት(8) የተለያዩ የቅድመ-ምረቃ መማሪያ ሞጅዩሎችን አዘጋጅቶ ጥቅምት18/2013 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
በሞጅዩል ምረቃ ስነ-ስርዓቱ የዩኒቨርሲቲውን አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮችና ምሁራን ተገኝተዋል፡፡ “ዩኒቨርሲቲያችን በአለምአቀፍ ደረጃ ምርጥ ከተባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመካተት ከቻለባቸው መስፈርቶች አንዱ ጥራት ያለው መማር ማስተማር ነው” ያሉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ደግሞ ጥራት ያለው ሞጅዩል መኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡
ሞጅዩሎቹ የጤና ኢንፎርማቲክስን ትምህርት ደረጃውን በጠበቀ እና ወጥ በሆነ መልኩ ለመስጠት አላማ አድርገው መዘጋጀታቸውን የህ/ጤ/ሳ/ ኮሌጁና አጠ/ስፔ/ሆስፒታሉ ምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የሞጅዩል ዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ዶ/ር ቢኒያም ጫቅሉ አብራርተዋል፡፡ ከተዘጋጁት ውስጥ 4000 (አራት ሺ) ሞጅዩሎች ለአስራ አምስት የሀገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች መሰራጨታቸውንም ዶ/ር ቢኒያም አክለው ገልጸዋል፡፡ የጤና መረጃን በቴክኖሎጂ ማዘመን ላይ ትኩረት አድርገው የተዘጋጁት ሞጅዩሎች ስምንት አይነት ሲሆኑ “Health Operations,Health Program, Routine Health Information System I &II, e-Health, Introduction to Health Informatics, Health Data Analytics and Data Quality and Information Use” የሚሉ ናቸው፡፡
በኮሚቴና በግል ሞጅዩሎቹን በማዘጋጀትና በማስተባበር ሂደት ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው አካላትም የእውቅና ሰርቲፊኬት ተሰጥቷል፡፡ *************************************************************
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት18/2013 ዓ.ም




