የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሶስት ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ በማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሦስት ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።ዩኒቨርሲቲው ትናንት ባደረገው ስብሰባ ለዶ/ር ታደሰ አወቀ፣ ለዶ/ር የማታው ወንዴ እና ለዶ/ር አሰግድ ደምሴ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ለኢዜአ ተናግረዋል።ዶ/ር ታደሰ አወቀ ላለፉት 14 ዓመታት በዩኒቨርሲቲው በባዮ ስታቲስቲክስና በፐብሊክ ሄልዝ የትምህርት ዘርፎች በመምህርነት ማገልገላቸው ተገልጿል።ከ100 በላይ የምርምር ስራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆኑ ጆርናሎች ለህትመት ያበቁ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በዳባት ከተማ ባቋቋመው የጤና ምርምር ጣቢያም በተመራማሪነት አገልግለዋል።ሌላው በክሊኒካል ሳይኮሎጂ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ዶ/ር የማታው ወንዴ ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲው በመምህርነትና በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃዎች ለ21 ዓመታት ያገለገሉ ናቸው።ዶ/ር የማታው 30 ያህል የምርምር ስራዎችን ያከናወኑና በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆኑ ጆርናሎችም ለህትመት ያበቁ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስረድተዋል።ሌላው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ደግሞ ከ18 ዓመታት በላይ በመምህርነትና በተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎቶች አስተዋጽኦ ያበረከቱት ዶ/ር አሰግድ ደምሴ ናቸው፡፡የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉhttps://www.youtube.com/c/EBCworldፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/EBCNEWSNOWበፎቶ የሚቀርቡ መረጀዎችን ለማግኘት ኢንስታግራም ገጻችንን ይጎብኙhttps://www.instagram.com/ebcnews1




