የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ከአፍሪካን ፊዩቸር ፋውንዴሽን” ጋር ስምምነት አካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምናው ዘርፍ ከጊዜ ወደጊዜ አስቸጋሪ እየሆነ የመጣውን የኩላሊት እጥበት ህክምና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ዩኒቨርሲቲያችን ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓትም የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የኩላሊት እጥበት ሕክምናውን (dialysis) ውጤታማ እንዳይሆን እያደረገው ይገኛል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ከአፍሪካን ፊዩቸር ፋውንዴሽን” ጋር በጋራ ለመስራት ሚያዝያ 8/2013 ዓ.ም በሴኔት አዳራሽ ስምምነት አካሂዷል፡፡ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲም በውይይቱ ተሳታፊ በመሆን የስምምነቱ አንድ አካል ሆኗል፡፡

የዚህ ስምምነት ዓላማ የኩላሊት እጥበት ህክምና አገልግሎትን ለማሻሻልና በቴክኒካዊ አሰራሮች ላይ እገዛ ለማድረግ ነው።
ስምምነቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይንን ጨምሮ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አስተባባሪዎች እና “የአፍሪካን ፊዩቸር ፋውንዴሽን” ተወካይ በተገኙበት ተካሂዷል።
የኩላሊት እጥበት ህክምና አገልግሎቱን በተግቢው መንገድ ለማከናወን የማሽኑን የቴክኒክ ጉዳይ በተመለከተ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኩል ሃሳብ የተነሳ ሲሆን “በአፍሪካን ፋውንዴሽን” በኩል ደግሞ በቴክኒካዊና አስተዳደራዊ አሰራሮች ላይ ስልጠና እንደሚሰጥ በተወካያቸው ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የስምምነት ሰነዱ የፊርማ ሥንስርዓት ተካሂዶ ውይይቱ ተጠናቋል።



