የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ኃይል
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲያችን የተቋቋመው ግብረ ኃይል ከተለያዩ የሙያ መስኮች የተዋቀረ ሲሆን በስካይፒ (skype) እየተገናኙ እና በኢሜይል በመላላክ የተግባር ሰነዶችን አዘጋጅተው አጠናቀዋል፡፡

ቫይረሱን ቀድሞ በመከላከል እና የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በመግታት ረገድ የጎንደር ማህበረሰብ ላይ መሰራት ያለባቸውን ዝርዝር ስራዎችንና ማስፈፀሚያ ስልቶች ለይቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቀጥታ ከሚያደርጋቸው ልዩ ልዩ ድጋፎች በተጓዳኝ ይህን ሙያዊ ግብረ ኃይል ያቋቋመው ኮረና ቫይረስ የሚያስከትለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ መቆጣጠር የሚያስችሉ አማራጮች ተግራዊ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትመጋቢት 30/2012 ዓ.ም



