የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ ‘ሀይል’ ምርምር ማዕከል አውደ ጥናት አካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሀይል ምርምር ማዕከል (Energy Research Center) በማቋቋም የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በማዕከሉ የሚሰሩ ከዘርፉ ጋር የተያያዙ የሳይንሳዊና የዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እውቀቶችንና ልምዶችን ማስተዋወቅ ዓለማው ያደረገ አውደ-ጥናት ሚያዚያ 29/2013 ዓ.ም በኢንስቲቲዩቱ ዲን ህንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዲን አቶ ሰለሞን መስፍን መርሀ-ግብሩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን የኢንስቲትቱ መምህራንና ከተለያዩ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲቲዎች የመጡ ተጋባዥ የዘርፉ ምሁራን በአውደ ጥናቱ ተሳትፈዋል፡፡




