የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አካሄዱ
ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከፌዴራል፣ አማራ ክልል እና ከዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ኮሮና ወረርሽኝን (COVID-19) ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራትን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ በአጠቃላይ ስፔሻላይድ ሆስፒታላችን የተዘጋጀውን የኮሮና በሽታ ማከሚያ ጣቢያ፣ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ክፍል እና የሳኒታይዘር ማምረቻ ማዕከልን ተመልክተዋል፡፡ በተጨማሪም በማራኪ ግቢ የሚገኘውን ወሸባ (quarantine center) እና ለይቶ ማቆያ (isolation center) ማዕከላትን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

ዶ/ር ሊያ በተሰሩ ስራዎች መደሰታቸውን ገልፀው በሱዳን አዋሳኝ በኩል የሚኖረውን ጫና ለመቋቋም የሚደረገው ጥረት በፌደራል ደረጃ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠውና ዩኒቨርሲቲውም ማዕከላዊ ጎንደርና መተማ አካባቢ ላከናወናቸው ተግባራት አመሰግነዋል፡፡
ህዝብ ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትግንቦት 08/2012 ዓ.ም



