የፕሮጀክት መክፈቻ ስነ ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል
ጎንደር ዩኒቨርስቲን ጨምሮ ሌሎች አራት ዪኒቨርሲቲዎች ከኢትዮጰያ (ሀዋሳ ዪኒቨርስቲ፣ ጂማ ዩኒቨርስቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ) እንዲሁም ሁለት ዩኒቨርስቲዎች እና አንድ የጤና ምርምር ተቋም ከኖርዌይ በጋራ በመፃፍ ያሸነፉት “Nurturing SDGs through Education Capacity Building in Ethiopia” የተሰኘ የስድስት አመት ፕሮጀክት የመክፈቻ ስነ ስርዓት በአካል እና በበየነ መረብ ዉይይት ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ነገም ቀጥሎ ይዉላል።
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የዩኒቨርስቲያችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደ ወይንን መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸው እንደገለፁት የዚህ ፕሮጀክት ይዘቶች በቅርቡ ከፀደቀዉ የዩኒቨርስቲው የ10 ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ጋር አብሮ የሚሄድ በመሆኑ ለመተግበር እንደማያስቸግር እና ለዉጤታማነቱም ተቋሙ ጠንክሮ እንደሚሰራ አስታዉቀዋል። የዚህ ፕሮጀክት የገንዘብ ምንጭ ኖራድ (NORAD) የተሰኘ በኖርዌይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር ያለ ኤጀንሲ ነዉ።





